እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!

እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን  የኬብሮንሂል ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ  አደራጅ ኮሚቴ ወደ ስራ ከገቡበት ቀን ጀምሮ የመተዳደሪያ ደንብ፣ የመመስረቻ ጽሁፍ፣ የተለያዩ ፖሊሲዎችን፣ የውስጥ አሰራር ማኑዋሎችንና ፎርማቶችን በመቅረጽ፣ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ላሉ ሰዎች የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀምና ሰፊ ገለፃዎችን በማድረግ እንደሀገር እንዲሁም እንደዓለም የተፈጠሩ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ውጫዊ  እና ውስጣዊ ሁኔታዎች ሳይበግሩት የአክሲዮን ሺያጮችን ለሁሉም ተደራሺ በማድረግ እየሰራ ይገኛል።  

በመሆኑም የተፈጠሩ ሀገራዊ የፀጥታ ችግሮች አሁን ላይ መለስተኛ መረጋጋት ከማሳየታቸው ጋር ተያይዞ የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገ ሲሆን ብሔራዊ ባንክ የሚጠይቃቸውን ቅድመ-ሁኔታዎችን በማሟላት ቅድመ ምስረታ ፈቃድ(Under formation license ) በማግኘት በተመረጡ አንጋፋ  የህዝብና  የመግንሥት  ሚዲያዎች አውታሮች (ቴለቪዥንና ሬዲዮ ጣቢያዎች) ላይ የማስታወቂያና ፕሮሞሽን ስራዎችን በስፋት በመስራት  ይበልጥ ለህዝብ ተደራሺ ለማድረግ  ዝግጅት አጠናቀናል። በመሆኑም በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን እያልን የኬብሮንሂል ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ መስራች አባላትና አመራሮች አመራሮች ተቋሙ እጅግ ባጠረ ጊዜ ውስጥ በቅርቡ ወደ ኦፕሬሽን ስራ ስለሚገባ ሁሉም አባላት አክሲዮን ከመግዛት ባሻገር ባላችሁበት ሥፍራ ሁሉ የተቋሙ ባለቤትና አምባሳደር እንደመሆናችሁ መጠን ሌሎች  እንደግል ፣ እንደቡድንና እንደተቋም ዕጣ በመግዛት የድርጅት ባለቤት የመሆን እድሉን እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር እንደአንድ አካልና አብሮ ሰራተኛ ከእኛ ጋር በነገር ሁሉ በታማኝነት ከጎናችን እንድትቆሙ ለማሳሰብ እንወዳለን። 

ኬብሮንሂል ማይክሮፋናንስ አክሲዮን ማህበር በዘርፉ በቂ እውቀትና ክህሎት ባላቸው  ባለሙያዎች ፣ የተለያዩ የዓለም አቀፍ የማይክሮ ፋይናንስና የሊደርሽፕ ስልጠናዎች በወሰዱት በዘርፉ ምሁራን የተደራጀ ተቋም በመሆኑ የንግድ ዓለሙን ሰብሮ በመግባት ተወዳዳሪ ከመሆን የዘለለ አሸናፊ በመሆን በበላይነት ዘርፉን ለመምራት ታላቅ የዓለም አቀፍ ራዕይ ሰንቆ ጉዞውን በይፋ ጀምሯል። በዚህ ብቻ አያበቃም ኬብሮንሂል ማይክሮፋናንስ አክሲዮን ማህበር ኦፕሬሽን በጀመረ ከሁለት ዓመት በኋላ ትላልቅ እህት ኩባንያዎችን ለመጀመር የአጭር ፣ መካከለኛና የረዥም ዓመት ዕቅዶች ተይዘው ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል። 

ስለዚህ ኬብሮንሂልን መምረጥ ከፍታን መምረጥ የመውጣት ጅማሬ ነው። ኑ አብረን እንሥራ አብረን እንደግ! ኬብሮንሂል አክሲዮን ማህበር 

ለኢትዮጵያ ትንሣኤ!

Share

Add Your Comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *